ሚኒስቴሩ
መግቢያ
በኢትዮጵያ ከትላልቅ እስከ መካከለኛ እርሻዎችን ለማልማት መስኖ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። ይሁን እንጂ ለአገሪቱ የግብርና ዘርፍ እና አጠቃላይ የኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ከሚፈጥረው ዕድል አንፃር ሲታይ አሁንም የሚጠበቀውን ያህል ጥቅም ላይ አልዋለም። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2023 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ባስቀመጠችው ግብ መሰረት የተፈጥሮ ሀብትና የመስኖ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ ያስችላታል።
ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን ሊፈታ የሚገባው ወሳኝ ጥያቄ የምግብ ዋስትና እና የአየር ንብረት መለዋወጥን የመቋቋም ጥያቄ ነው። የመስኖ ቴክኖሎጂ ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ከዋለ ይህን ችግር ለመፍታት የሚረዳና በሌሎችም ዘርፎች አዎንታዊ ውጤት ሊኖረው የሚችል አማራጭ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ጥያቄ በአገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች ከሚገኙ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ጋር የተያያዘ ነው። የኢትዮጵያ ቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች ሊሰጡ የሚችሉት ጥቅምና ዕድሎች በመጠን ብዙ ቢሆኑም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጥልቀት ተመርምረው ያልሰፈሩ ናቸው።
ስለሆነም በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኘውን ሰፊ መሬት፣ ውሃ፣ እንስሳትና የሰው ሀብት በመጠቀም አገሪቱ የልማት ተልዕኮዋን እንድታሳካ የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ተቋቋመ።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
ራዕይ
የእኛ ራዕይ ዘላቂና በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ፣ ለአየር ንብረት መለዋወጥ የማይበገር የመስኖ ልማትን በመተግበር የምግብ ሉአላዊነትና ዋስትናን በማረጋገጥ እንዲሁም የቆላማና አርብቶአደር አካባቢዎች ልማትና አስተዳደርን በማጠናከር የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት ነው።
About
Message from the Minister
Ethiopia stands at the forefront of a transformative journey, one that seeks to secure our nation’s food sovereignty and achieve self-sufficiency. The establishment of the Ministry of Irrigation and Lowlands (MILLs) signals a bold step forward in our pursuit of these noble objectives.
In Ethiopia, agriculture is the backbone of our economy. However, the potential for optimizing irrigation remains largely untapped, with less than 10% of arable land currently benefiting from such systems. Recognizing the critical importance of these sector, the Ministry of Irrigation and Lowlands (MILLs) has undertaken an ambitious mission to implement innovative, efficient, and sustainable irrigation systems that will revolutionize our agricultural landscape.In addition to enhancing irrigation, developing Ethiopia’s lowlands is one of our top priorities. By implementing targeted development strategies, we can unlock the productivity of lowlands, ensuring they contribute significantly to our national food security and economic resilience.Our ministry is dedicated to fostering innovation, sustainability, and collaboration. Together, we can transform Ethiopia’s agricultural sector, ensuring a prosperous future for all. As we move forward, I would like to invite our governmental counterparts, the private sector, and development partners to join us in these transformative efforts to achieve food sovereignty, and lowland development while advancing several Sustainable Development Goals (SDGs).Together, let us stride towards a future where every Ethiopian can blossom and thrive.
H.E. Abraham Belay Berhe (PhD)Minister of Irrigation and LowlandsFederal Democratic Republic of Ethiopia
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
የሚኒስቴሩ መዋቅር
የሚኒስትር ጽ/ቤት
ዋና ስራ አስፈጻሚ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
ተልዕኮ
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተልዕኮ ዘመናዊ የመስኖ ስርዓትን በመተግበር እና ድርቅን የመቋቋም አቅምን በማጎልበት ለቆላማው የኢትዮጵያ ክፍል ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለውን ራዕይ ማሳካት ነው። እንዲሁም የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህልውና በማያናጋ መልኩ ውሃን እንደ ቁልፍ ሃብትና ግብአት በመጠቀም ሁለንተናዊና የተቀናጀ ዘላቂ ልማትና አስተዳደርን ለማስፈን ሚኒስቴሩ ተግቶ ይሰራል።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
መመሪያ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በአዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት መዋቅር በአዋጅ ቁ. 1263/2021 መሰረት የተቋቋመ አዲስ ሚኒስቴር ነው። ሚኒስቴሩ የተቋቋመው በውሃ-ኢነርጂ መሠረተ ልማቶች መካከል የነበረውን ክፍተት ለማጥበብ እና አስፈላጊውን የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ነው። በመሆኑም በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ዘላቂ ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የምግብ ሉዓላዊነትን፣ የምግብ ዋስትናና የኑሮ መሻሻልን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት መስኖ እንዲሁም የቆላማ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ወደ ሚኒስቴር ተቋምነት አድገዋል።
በአዋጁ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚከተሉትን ሥልጣና ተግባራት ይኖሩታል፦
አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያስተባብራል፤
በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በውሃና ኤነርጂ ሚኒስቴር ጥናት የተለዩ የሀገሪቱን የከርሰ ምድር እና የገጸ-ምድር የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት የሚውልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያገኙ በተለያዩ ዘዴዎች ያስተዋውቃል፤ ሕግን መሠረት በማድረግ ባለሀብቶች ማትጊያ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
ከግብርና እና ውሃና ኤነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባባር የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ውሃን ማዕከል ያደረጉ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ የመስኖ ልማቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤
በተፋሰሶች ውስጥ የሚደረጉ የመስኖ ማስፋፋት ሥራዎችን ለመደገፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፤
የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ምርታማነት በሚያሳድጉ ወቅታዊ ቴክኖሎጂዎች እንዲደገፉና ውሃ ቆጣቢ አሠራር እንዲከተሉ ያበረታታል፤