ወደ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ድረ-ገፅ እንኳን በደህና መጣችሁ። የመስኖ ልማት በምግብ አቅራቦት ራስን ለመቻልና ድህነትን ለመዋጋት ግንባር ቀደም ከሆኑት ስትራቴጂዎች/ስልቶች አንዱ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን የምግብ ሉዓላዊነትና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል። የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴርም ይህንን ዓላማ ለማሳካት ሃገር አቀፍ የመስኖ ስልት በማልማት ላይ ይገኛል።
የሚኒስቴሩ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ክንፍ በዋናነት የሀገሪቷን የመስኖ አቅም በመመርመር፣ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማጥናትና በመንደፍ መሠረተ ልማቶችን የመገንባት፣ መርሃ ግብሮችን የማስተዳደር እና የማስኬድ ኃላፊነት አለበት።
ሚኒስቴሩ ምርታማነትን በሚያሻሽሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ከሀገር አቀፍ የልማት ዕቅድ ጋር ተጣጥመው የሚሄዱ የመስኖ መርሃ ግብሮችን የማዘጋጀት ሃላፊነትና ዕቅድ አለው። ሚኒስቴሩ ለመስኖ ፕሮጀክቶች ስኬታማነት አስፈላጊውን የአቅም ግንባታና የቴክኒክ ድጋፍ በማቅረብ ከክልል መንግስታት ጋር በቅርበት ይሰራል።
ሚኒስቴሩ የመስኖ ፖሊሲን የቁጥጥር ማዕቀፍ እና የመርሃ ግብሮች ልማትን የማዘጋጀት ከፍተኛ ድርሻን የሚወስድ ቢሆንም የግሉ ሴክተር ሚና በተለይ አነስተኛ መጠን የመስኖ መፍትሄዎችን በማቅረብ እና መካከለኛ መጠን የመስኖ መርሃ ግብሮችን በማስተዳደር ረገድ ወሳኝ ነው። ይህን በማስመልከት ሚኒስቴሩ በሕገ መንግስቱ መሠረት የመስኖ ኢንቬስተርስ፣ የየአካባቢው ማህበረሰቦች በመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ማበረታቻዎችን እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ስለዚህ የግል ድርጅቶች፣ ለጋሾች እና የተለያዩ ተቋማት ባለድርሻ አካላት በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ምርት ለማሻሻል እንዲተባበሩን እንጋብዛለን።
ከአክብሮት ጋር