ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ እና ልዑካንን ተቀብለው በቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

In NewsJune 5, 20241 Minute

Month: June 2024

ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም.

ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የመስኖ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በተባበሩት መንግስታት የምግብና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሰርቪስ ሃላፊ ጂዮቫኒ ሙኖዝ፣ በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ እና ልዑካንን ተቀብለው በቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው በመጪ ፍላግሺፕ ፕሮጀክቶቻችን ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ማቅረብ፣ የመስኖ ኮዶችን፣ መመሪያዎችን እና የሕግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ላይ ሲሆን #FAO በጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ MIS (Management Information System) ስርአቶችን ከፕሮጀክቶቹ ጋር በማዋሃድ የመረጃ አያያዝ አቅማችንን ማጎልበት ላይ አብሮ ለመስራት ተስማምቷል። በተጨማሪም ቡድኑ ለመስኖ ዲዛይን፣ ለግንባታ፣ ለአሰራር እና ለጥገና እንዲሁም የመስኖ ኢንቨስትመንት ትንተና እና የታሪፍ መቼቶች ላይ ያተኮረ ድጋፍ ላይ ተወያይተዋል።

ሚኒስቴራችን ከFAO ጋር ያለው ትብብር የግብርና መሠረተ ልማትን እና ዘላቂነትን ለማጎልበት በምናደርገው ጥረት ትልቅ ሚና ይጫወታል።