The submission Method and Date of kalid Dijo Irrigation Development Project Bid number of MILL-ICP-W-0004-2017 has been changed.Please refer to the attached picture letter.January 23, 2025 የአልዌሮ ግድብ ለታለመለት የመስኖ ልማት ማዋል የሚቻልበትን ሁኔታ ለማየት በዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና በክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ዑምድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የፌደራል እና የክልል አመራሮችና ሙያተኞች ቡድን ጉብኝት አካሂደዋል :: የአልዌሮ ግድብ ከተገነባ ከሰላሳ አመት በላይ ሲሆን 10,000 ሄክታር በመስኖ ለማልማት ታስቦ የተገነባ ግድብ ነው :: ሆኖም እስካሁን ድረስ ከ1500 ሄክታር በታች እያለማ የታለመለትን ያክል ምርት ሳይሰጥ መቆየቱን በጉብኝቱ ወቅት ተገልፆል:: የግድቡ የተለያዩ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ በጥልቀት በማጥናት አስፈላጊ የጥገና ስራን በማከናወን ወደ ሙሉ አቅሙ መመለስ እንዲቻል እና ከመስኖ ልማት ጎን ለጎን የአሳ ሃብትን የማልማት ሂደት ለማዘመን እንደሚሰራ ሚኒስትሩ ገልፀዋል ::October 16, 2024 አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ መስከረም 27/2017 በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። የፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡October 7, 2024 ለመላው ኢትዮጵያውያን/ት ለትውልደ ኢትዮጵያዊያንና/ት የ2017 ዓ.ም ከብረት የጠነከረ የአንድነትና የህብረት አመት እንዲሆንልን እየተመኘሁ !! በርካታ ሀሳቦቻችንን በብርቱ ፈተናዎች ውስጥ ጭምር አልፈን በማድረግ ማሳካት የጀመርናቸውን ጅምሮች ወደ መደምደሚያ የምናመጣበት፤ አዳዲስ ትልሞቻችንና የአካታች ብልጽግና ግቦቻችንን በብቃት ተባብረን የላቁ ደረጃዎችና እመርታዎች የምናሰፈጽምበት፤ የስራና የፍሬ ዘመን ያድርግልን ስል በራሴና በመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች ስም መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።September 11, 2024 Today, H.E. Dr. Abraham Belay, Minister of Irrigation and Lowlands, welcomed Frauke Jungbluth, Practice Manager for Agriculture and Food, and her team, who have been managing the LLRP I project and will be overseeing LLRP II from the World Bank’s side. We are excited about the opportunities ahead and look forward to exceeding the substantial success under the LLRP I project. #MILLs #WorldBank #LLRP #Lowlands #IrrigationSeptember 7, 2024 የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ ******************* የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር ዶ/ር እንድርያሥ ጌታ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ እንዳሉት የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በማምጣት ስኬታማ ለመሆን ነው፡፡ በተጨማሪም በሃብት አጠቃቀምና በስራ ዲሲፕሊን እንዲሁም በተkማዊና ሃገራዊ ተልዕኮ ላይ ግልፅነትን በመፍጠር በጋራ መግባባትና በመቀናጀት የ2017 በጀት ዓመት እቅድን ውጤታማ የሚናደርግበት ነው ብለዋል፡፡ ሚ/ር መ/ቤቱ አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ እያከናወነ ያለበትና በዚህም የተሸለ አመራር መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም አዲሱ ዓመት የሰላም &የጤናና የደስታ እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵ ዊያንና ለሚ/ር መ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ተመኝተዋል፡፡ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም.September 5, 2024 ዛሬ ወደ መስኖና ቆላማ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ የተመደቡትን አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና አቶ አብዱርሃማን አብደላ የእንኳን ደህና መጣቹ አቀባበል ተደረገላቸው :: በሂደቱ ከአጠቃላይ የሚኒስቴር መስራቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ማናጅመንት አባላት ትውውቅ አድርገዋል :: በፕሮግራሙ በክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ የተቋሙን አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ስራዎች ዝርዝር የስራ መመርያ ለሁሉም አመራሮች ተሰጥተዋል ::September 2, 2024 በ2017 በጀት ዓመት የጊዳቦ መስኖ መሬት ዝግጅት ፕሮጀክት ግንባታን 25 % ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለቤትነት በኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች አዋሳኝ ቦታ የሚገነባው የጊዳቦ መስኖ መሬት ዝግጅት (ሁለተኛና ሶስተኛ ቦዮች ) ግንባታ ፕሮጀክት በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ የፕሮጀክቱን 25 % ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡ የጊዳቦ መስኖ መሬት ዝግጅት ግንባታ ፕሮጀክት 13 ሺህ ሄክታር የማልማት አቅም ያለውና 26 ሺህ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ፕሮጀክቱ የተጀመረው በ2016 ዓ/ም የካቲት ወር ሲሆን በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅደዋል፤፤ የፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ሲሆን አማካሪ ድርጅቱ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 3.33 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ/ምSeptember 2, 2024 H.E. Abraham Belay (PhD), Minister of Irrigation and Lowlands received Mr. Donal Brown, IFAD Associate Vice President, along with senior delegates from IFAD, for discussions on ongoing projects and the successful completion of LLRP I. Mr. Brown emphasized the significance of this partnership as the largest in Africa and one of IFAD’s most effective collaborations. He expressed gratitude to the Ethiopian government for its transformative and recent Economic Reform Policy and expressed optimism about increasing resource allocations to support ongoing and future initiatives, including MILLs’ groundbreaking Climate-Resilient Irrigation for Sustainable Production (CRISP) and Small-Scale Irrigation projects. The honorable minister highlighted the recent fast-paced progress of our projects, emphasizing irrigation as a key entry point for driving agricultural transformation. Both parties noted the need to incentivize private sector investments in irrigation that align with these initiatives.August 30, 2024 H.E. Abraham Belay (PhD), Minister of Irrigation and Lowlands, received the newly appointed Country Director for WFP Ethiopia, Mr. Zlatan Milišić, for a courtesy meeting. Both parties discussed potential collaborations on livelihood improvement projects, sustainable small-scale irrigation, and market-driven interventions. #MILLs #WFP #CollaborationAugust 29, 2024 Newsletter Subscribe to be part of our updates, insights and journey!