በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (#LLRP) የፌዴራል ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ እየተካሄደ ነው። ———————————- በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የፌዴራል ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ እንዲሁም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር እንድርያስ ጌታ እና የሚኒስቴር መ/ቤቱና የባለድርሻ መ/ቤቶች የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር እንድርያስ ጌታ የፌዴራል ስትሪንግ ኮሚቴው የፕሮጀክቱ ምዕራፍ አንድ ማጠናቀቀቂያ እና ውጤትን የሚገመገምበት እንዲሁም የምዕራፍ ሁለት ዕቅድ የሚዳሰስበት እንደሆነ ገልፀዋል። የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር LLRP I ለቆላማ አካባቢ ነዋሪዎች ዘላቂ የኑሮ ሁኔታ ለውጥ ያመጣበት መሆኑን የምናረጋግጥበት በተጨማሪም የፕሮጀክቱን ምዕራፍ ሁለት (LLRP II) ወደ መሬት ለማውረድ ሁሉም ባለድርሻ ተቋማት ሃላፊነት ወስደን የምንሰራበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡ —- LLRP II በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በ424 ሚሊዮን ዶላር በ7 ክልሎለች እና ድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ 120 ወረዳዎች የሚተገበር ሲሆን፣ 3 ሚሊዮን የቆላማ አካባቢ ነዋሪዎችን (600ሺህ አባወራዎችን፣ 50% ሴቶች፣ 30% ወጣቶች) ተጠቃሚ ያደርጋል። የፕሮጀክቱ ዓላማ በሃገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ሕይወት ለማሻሻል የሚያግዙ ተግባራት ማጠናከር ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች እና አማራጭ የገቢ ምንጭ መፍጠር ላይ የሚሰራ ሲሆን ኢትዮጵያ ምርታማነትን ለማሳደግ በምታደርገው እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም | ቢሾፍቱ

የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ ****************************************** የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ በጎፋ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ ምክንያት በወገኖቻችን ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት በመድረሱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለፅ ፈጣሪ የሞቱትን ነፍሳቸውን እንዲምር ተመኝተዋል። ጉዳቱ የሁላችን የኢትዮጵያውያን መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል። የክልሉ መንግስትና የዞኑ አስተዳደር በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውንና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን በቋሚነት ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ የ5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መደረጉን አመልክተው ድጋፉን ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አስረክበዋል። በቀጣይ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገው ተግባር እስኪጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብተዋል። የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እስከ ቦታው ድረስ በመሄድ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋቸው በዞኑ አስተዳደር እና በተጎጂዎች ስም አመስግነዋል። ተጎጂዎችን እና ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ በመሆኑ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዋና አስተዳዳሪው ጠይቀዋል።

በራሪ ጽሑፍ

የግንዛቤዎችና የጉዞአችን አካል ለመሆን ይመዝገቡ!

    የባለቤትነት መብት © 2023 የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር  መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።